ቀጥታ፡

በተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች የትምህርት እድል ያገኙ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች የኢትዮጵያን መካነ ርዕይ ጎበኙ

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 01/2016 (ኢዜአ)፦በተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች የትምህርት እድል አግኝተው በመማር ላይ ያሉ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ዛሬ በዱባይ ኤክስፖ ሲቲ የሚገኘውን የኢትዮጵያ አረንጓዴ አሻራ መካነ ርዕይ(Pavilion) ጎብኝተዋል።

በጉብኝቱም ኢትዮጵያ በአየር ንብረት ለውጥ በዓለም አቀፍ ደረጃ እያደረገች ያለውን እንቅስቃሴ በተመለከተ ገለፃ እንደተደረገላቸው ከተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የኢትዮጵያ ቆንስላ ጄኔራል ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡


 

በ28ኛው የዓለም የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ላይ የተሳተፉ የበርካታ ሃገራት መሪዎችና እንግዶች ይሄንን መካነ ርዕይ በመጎብኘት ኢትዮጵያ በአረንጓዴ አሻራ ልማት እያከናወነች ያለውን ጥረት ማድነቃቸው ይታወሳል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም