18ኛው የብሄር ፣ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ቀን በተለያዩ የኢትዮጵያ ሚስዮኖች ተከበረ - ኢዜአ አማርኛ
18ኛው የብሄር ፣ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ቀን በተለያዩ የኢትዮጵያ ሚስዮኖች ተከበረ
አዲስ አበባ፤ ህዳር 30 / 2016(ኢዜአ) ፡- የኢትዮጵያ የብሄር ፣ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ቀን በኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ሚስዮኖች እና ቆንፅላ ጽህፈት ቤቶች በተለያዩ መርሃግብሮች ተከብሯል።
በናይሮቢ ፣ ካምፓላ ፣ ዱባይ ፣ ፓሪስ እና ሮም በሚገኙት የኢትዮጵያ ሚስዮኖች እና ቆንፅላ ጀነራል ጽህፈት ቤት በዓሉን በተለያዩ ዝግጅቶች አክብረዋል።
በዝግጅቶቹ በየአካባቢው የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ተሳታፊ ሲሆኑ የኢትዮጵያን ብዝሃነት የሚያሳዩ መርሃግብሮችም መቅረባቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
የብሄር ብሄርሰቦችና ህዝቦች ቀን ለ18 ተኛ ግዜ "ብዝሃነት እና እኩልነት ለሀገራዊ አንድነት" በሚል መሪ ሀሳብ በትናንትናው ዕለት በሶማሌ ክልል አስተናጋጅነት በጅግጅጋ ከተማ ተከብሯል።