ኢትዮጵያ በሱዳን ያለው ግጭት በሰላም እንዲቋጭ የሚደረገውን ጥረት በፅኑ ትደግፋለች - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

አዲስ አበባ ፤ ህዳር 29/2016 (ኢዜአ) ፦ ኢትዮጵያ በሱዳን ያለው ግጭት በሰላም እንዲቋጭ የሚደረገውን ጥረት በፅኑ ትደግፋለች ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ወንድሜ ፕሬዝዳንት እስማኤል ኦማር ጊሌ በሱዳን ጉዳይ ላይ የተካሄደውን 41ኛውን የኢጋድ ልዩ የመሪዎች ጉባኤ በማስተናገዳቸው ምስጋናዬን አቀርባለሁ ብለዋል፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ባወጣው መረጃ ደግሞ ኢትዮጵያ በኢጋድ የሚደረገውን የሰላም እና መረጋጋት ሂደት በንቃት በመደገፍ ላይ መቆየቷ አስታውቋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩና የልኡካን ቡድናቸው ተሳትፏቸውን አጠናቀው ዛሬ ማምሻውን ወደ አዲስ አበባ መመለሳቸውንም ጽህፈት ቤቱ ገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም