የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል ኢትዮጵያን ለማበልጸግ የሰነቅነውን ራዕይ ዕውን ለማድረግ የገባነውን ቃል የምናድስበት ቀን ነው - ከንቲባ አዳነች አቤቤ - ኢዜአ አማርኛ
የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል ኢትዮጵያን ለማበልጸግ የሰነቅነውን ራዕይ ዕውን ለማድረግ የገባነውን ቃል የምናድስበት ቀን ነው - ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ ፤ ህዳር 29/2016 (ኢዜአ) ፦ የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል ኢትዮጵያን ለማበልጸግ የሰነቅነውን ታላቅ ራዕይ ዕውን ለማድረግ የገባነውን ቃል ኪዳን የምናድስበት ቀን ነው ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።
18ኛዉ የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል "ብዝኃነትና እኩልነት ለሀገራዊ አንድነት" በሚል መሪ ሀሳብ በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ እየተከበረ ይገኛል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በጅግጅጋ በድምቀት እየተከበረ ለሚገኘው ለ18ኛዉ የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት የመልካም ምኞት መልዕክታቸው ይህ ዕለት በብዝሀነት ውስጥ አንድነት የሚደምቅበት፣ ሕብረ ብሔራዊ ወንድማማችነትና እህትማማችነት ያስተሳሰረን ህዝቦች በድምቀት በጋራ የምናከብርው፣ በልዩነቶች ውስጥ ያለው አንድነት ጎልቶ የሚታይበት ነውም ብለዋል።
ከንቲባዋ አክለውም በዓሉ ኢትዮጵያን ለማበልጸግ የሰነቅነውን ታላቅ ራዕይ ዕውን ለማድረግ የገባነውን ቃል ኪዳን የምናድስበት ቀን ነው ሲሉም ገልጸዋል።
ኢትዮጵያዊነት አንድ ዓይነትነት አይደለም፤ ኢትዮጵያዊነት መለያየትም አይደለም፤ ኢትዮጵያውያን ከሚለያዩን ጉዳዮች ይልቅ በአንድነት ያጋመዱን ጉዳዮች ይበዛሉ ሲሉም አክለዋል ከንቲባዋ።
ኢትዮጵያዊነት መጠሪያችን ብቻ ሳይሆን፣ ማንነታችንም ነው ያሉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ መልካም በዓል ይሁንልን ሲሉም የመልካም ምኞት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።