ቀጥታ፡

18ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል በተለያዩ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ.ሚስዮኖች እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፤ ህዳር 29/2016 (ኢዜአ)፦‘’ብዝኃነትና እኩልነት ለሀገራዊ አንድነት’’ በሚል ሀሳብ የሚከበረው 18ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ሚስዮኖች በተለያዩ ስነ-ስርአቶች በመከበር ላይ ነው።

በዓሉን ካከበሩት መካከል በጅቡቲ፣ ካይሮ ፣ ቴል አቪቭ ፣ ኢስላማባድ እንዲሁም ሪያድ ሚገኙት የኢትዮጵያ ሚስዮኖች ይጠቀሳሉ።


 

በክበረ በዓሉ ላይ በየሚሴዮኖቹ ከሚገኙት ዲኘሎማቶች እና ሰራተኞች በተጨማሪ በየሃገራቱ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆችም ተሳታፊ ሆነዋል።


 

የኢትዮጵያን ባህል ፣ ትውፊት እና ታሪክ የሚያስተዋውቁ ዝግጅቶችም በመርሃ ግብሮቹ ላይ መቅረባቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም