ቀጥታ፡

18ኛው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በጅግጅጋ ከተማ በመከበር ላይ ይገኛል

አዲስ አበባ፤ ህዳር 29/2016 (ኢዜአ)፦ 8ኛው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል ዛሬ ከማለዳ ጀምሮ በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ በተለያዩ ሁነቶች እየተከበረ ይገኛል።

በመርኃ ግብሩ የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አደም ፋራህ፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገርን ጨምሮ የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮችና የከተማ አስተዳደር ከንቲባዎች፣ ከፍተኛ የፌደራልና የክልል የሥራ ኃላፊዎች፣ የኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች የባህል ቡድኖች ታድመዋል።

'ብዝሃነትና እኩልነት ለሀገራዊ አንድነት' በሚል መሪ ሀሳብ የሚከበረው በዓሉ ሀገራዊ አንድነትና ሕብረ ብሔራዊነትን ሊያጠናክር በሚያስችል መልኩ እንደሚከበር ተገልጿል።


 

ባለፉት አራት ቀናት ማለትም ኅዳር-25፣ 26 ፣ 27 እና 28 በቅደም ተከተል የወንድማማችነት፣ የብዝኃነት፣ የአብሮነት እንዲሁም ትላንት የመደመር ቀን በሚል መሪ ሃሳብ በተከታታይ ቀናት ሲከበር የምክክር መድረክ እና የጎዳና ላይ የባህል ትርዒቶችም ተካሂደዋል።

ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ልምዳቸውን፣ ተሞክሯቸውን፣ ባህላቸውን፣ እሴቶቻቸውን የተለዋወጡባቸው መርሐ ግብሮችም ተዘጋጅተዋል።

የጅግጅጋ ከተማ በዓሉን ለመታደም ለመጡ እንግዶች በተለያዩ ዘርፎች ዝግጅት በማድረግ ቀልጣፋ አገልገሎት እየሰጠች ቆይታለች።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም