ኢትዮጵያ ለጅቡቲ የላከችው 100 ሺህ ችግኞች ጂቡቲ ደርሷል - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ ለጅቡቲ የላከችው 100 ሺህ ችግኞች ጂቡቲ ደርሷል
አዲስ አበባ ፤ ህዳር 28/2016 (ኢዜአ) ፦ በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር አዘጋጅነት ዘንድሮ ለሦስተኛ ጊዜ ኢትዮጵያ ለጅቡቲ የላከችው 100 ሺህ ችግኞችን የያዘ ጭነት ዛሬ ረፋድ ላይ ጂቡቲ ደርሷል ።
የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ልዑክ ጅቡቲ ሲደርሱ በጂቡቲ የኢትዮጵያ አምባሳደር ብርሃኑ ጸጋዬ እና በጅቡቲ የስራ ኃላፊዎች አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
ኢትዮጵያ ከጎረቤት አገሮች ጋር ካላት ዘርፈ ብዙ የልማት ትስስር ባሻገር የአረንጓዴ አሻራ ዲፕሎማሲ ላይ መስራት የጋራ ኃላፊነት የሚያሳይ ትልቅ ተግባር መሆኑ ተገልጿል።
ኢትዮጵያ እስከ 2014 ዓ.ም በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር 200 ሺህ ችግኞችን ለጎረቤት አገራት ማበርከቷ ይታወሳል።
በዚህ በቀጣይም ለሌሎች ጎረቤት አገራት ችግኞችን ለማድረስ ባቀደችው መሰረት
ዘንድሮም ለሦስተኛ ጊዜ 100 ሺህ ችግኞችን ወደ ጅቡቲ መላኳን በጅቡቲ ከኢትዮጵያ ኤምባሲ የተገኘው መረጃ አመልክቷል።