ቀጥታ፡

የክልሎች ርዕሳነ-መስተዳድሮችና የሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች ከንቲባዎች በ18ኛው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል ላይ ለመታደም ጂግጂጋ ገብተዋል

አዲስ አበባ ፤ ህዳር 28/2016 (ኢዜአ)፦ በ18ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን በዓል ላይ ለመታደም የተለያዩ ክልሎች ርዕሳነ-መሥተዳድሮች እና የሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች ከንቲባዎች ጂግጂጋ ገብተዋል፡፡

ርዕሳነ-መስተዳድሮቹና ከንቲባዎቹ ጂግጂጋ ከተማ ሲገቡም የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሐመድና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች አቀባበል እንዳደረጉላቸው ከፌዴሬሽን ምክር ቤት የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

ርዕሳነ-መስተዳድሮቹና ከንቲባዎቹ ወደ ጂግጂጋ ያቀኑት በ18ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል ላይ ለመታደም መሆኑም በመረጃው ተመላክቷል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም