ቀጥታ፡

የዓለም የጥቁር ህዝቦች የታሪክ፣የቅርስና የትምህርት ማዕከል የመክፈቻ ስነ ስርዓት ዛሬ ይካሄዳል

አዲስ አበባ፤ ህዳር 28/2016 (ኢዜአ)፡- የዓለም የጥቁር ህዝቦች የታሪክ፣የቅርስና የትምህርት ማዕከል የመክፈቻ ስነ ስርዓት በአፍሪካ ህብረት አዳራሽ በዛሬው ዕለት ይካሄዳል። 

በመክፈቻ ስነ ስርዓቱ ላይ ከፍተኛ የመንግስት ስራ ኃላፊዎች፣ የማዕከሉ መስራች አባላት፣ የዲፕሎማሲ ማህበረሰብ ተወካዮች፣ የሲቪክ ማህበራት ተወካዮችና ሌሎች ተጋባዥ እግዶች እንደሚገኙ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል። 

ማዕከሉ ዋና መቀመጫውን በኢትዮጵያ ማድረጉ ኢትዮጵያ የጥቁር ህዝቦች ቤት መሆኗን አዲስ አበባ ደግሞ የዲፕሎማሲ ማዕከልነቷን የሚያፀና ነው። የማዕከሉ መቀመጫ በአዲስ አበባ መከፈት ኢትዮጵያ ለጥቁር ህዝቦች ነፃነት ላበረከተችው ጉልህ አስተዋጽኦ እውቅና የሚሰጥ ነው።

የማዕከሉ መከፈት ዲፕሎማሲያዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ፋይዳው የጎላ ከመሆኑም በላይ የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲ ስኬት አንዱ ማሳያ መሆኑን የውጭ ጉዳይ አስታውቋል።  
 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም