ቀጥታ፡

የብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በዓል የአንድነታችን ማሳያና የውበታችን መገለጫ መድረክ ሆኗል  

አዲስ አበባ ፤ ህዳር 27/2016(ኢዜአ)፦  የብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በዓል የአንድነታችን ማሳያና የውበታችን መገለጫ መድረክ ሆኗል ሲሉ የበዓሉ ታዳሚዎች የባህል ቡድን አባላት ገለጹ።

18ኛው የብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን ከኅዳር 25 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ በጅግጅጋ ከተማ በተለያዩ መርሃ-ግብሮች እየተከበረ ነው። 

ከሁሉም የሀገሪቷ አካባቢዎች ታድመው ጅግጅጋ ከተማ የሚገኙ የባህል ቡድን አባላት "የአብሮነት ቀንን" በተለያዩ ትዕይንቶች በደማቅ ሥነ-ሥርዓት አክብረዋል። 

ኢዜአ ያነጋገራቸው የባህል ቡድን አባላት በጅግጅጋ እየተከበረ ባለው የብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በዓል ከአቀባበል ጀምሮ አስደናቂና አስደሳች መሆኑን ገልፀዋል።

የብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በዓል የአንድነታችን ማሳያና የውበታችን መገለጫ መድረክ ሆኗል ሲሉ ተናግረዋል። 

በዓሉን በአንድነትና ሕብረ-ብሔራዊ ድምቀት እያከበርን  በመሆኑ ተደስተናል ያሉት አስተያየት ሰጪዎቹ እሴቱን ጠብቀን የሀገር ኃብት ሆኖ እንዲቀጥል መሥራት አለብን ብለዋል።

በክብረ-በዓሉ አከባበር አንዱ የሌላውን ባህል በመጋራት በአንድነት፣ በፍቅርና አብሮነት እያከበርን ነው ሲሉ ተናግረዋል። 

18ኛው የኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በዓል "ብዝኃነትና እኩልነት ለሀገራዊ አንድነት" በሚል መሪ ሃሳብ በተለያዩ ዝግጅቶች በጅግጅጋ ከተማ በድምቀት መከበሩን ቀጥሏል።

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም