ቀጥታ፡

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር  በሴቶች ኢኮኖሚ ተጠቃሚነት  ላይ  ከቢል እና ሚሊንዳ ጌትስ  ፋውንዴሽን ጋር ኢትዮጵያ  በትብብር ለመስራት ዝግጁ መሆኗን ገለጸ

አዲስ አበባ ፤ ህዳር 27/2016(ኢዜአ) ፦የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር  በሴቶች ኢኮኖሚ ተጠቃሚነት  ላይ  ከቢል እና ሚሊንዳ ጌትስ  ፋውንዴሽን ጋር ኢትዮጵያ  በትብብር ለመስራት ዝግጁ መሆኗን ገለጸ።

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ  እንዳሉት ቢል እና ሚሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን በደቡብ እስያና ከሰሐራ በታች የአፍሪካ ሀገራት የሴቶችን ኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ለማሳደግ ከሚሰራው ፕሮጀክት  ጋር ኢትዮጵያ በትብብር ለመስራት ዝግጁ  ናት።

ሚኒስትር ዴኤታዋ  የቢል እና ሚሊንዳ  ጌትስ ፋውንዴሽን የሴቶች ኑሮ መተዳደሪያ ልማት ምክትል ዳይሬክተር ሌሳ ሽራደር ጋር በፕሮጀክቱ ትግበራ ዙሪያ ተወያይተዋል፡፡



 

በኢትዮጵያ የሴቶችን ማህበራዊ ህይወት ለማሻሻል እንቅፋት የሆነው የስራ መነሻ ካፒታል እጥረት መሆኑን  ገልጸዋል።

ይህንን ችግር ለመቅረፍ ፋውንዴሽኑ ድጋፍ እንዲያደርግ ጠይቀዋል። 

ፕሮጀክቱ ትክክለኛ መረጃ እንዲኖር ፣ ሴቶች የፋይናንስ አቅርቦት እንዲያገኙ ፣ አካታች ዲጂታል መሳሪያዎችን ለሴቶች ተደራሽ ማድረግ፣ የተሻለ ገበያ መፍጠር እና የህፃናት እንክብካቤ የሚሉትን ምሰሶዎች መያዙን አብራርተዋል።

ተግባራቱ ከኢትዮጵያ ፖሊሲና ፕሮግራሞች ጋር የተስማሙ ስለመሆናቸው አንስተዋል። 


 

የቢል እና ሚሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን የሴቶች ኑሮ መተዳደሪያ ልማት ምክትል ዳይሬክተር ሌሳ ሸራደር ፋውንዴሽኑ የሴቶችን ማህበራዊ ህይወት ለማሻሻል ኢትዮጵያ የምታደርገውን ጥረት እንደሚደግፍ አረጋግጠዋል። 

ፋውንዴሽኑ በ2ዐ3ዐ  ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው 8ዐ ሚሊየን በደቡብ እስያና የሰብ ሰሐራ አፍሪካ ሴቶችን ኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ለማሳደግ የሚያስችል ፕሮጀክት ቀርፆ ወደ ስራ ገብቷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም