ቀጥታ፡

በአዲስ አበባ የንብረት አስተዳደርና አጠቃቀም በዲጂታል ቴክኖሎጂ አሰራር ለመተግበር የሚያግዝ ሶፍትዌር ወደ ስራ ገብቷል

አዲስ አበባ ፤ ህዳር 27/2016 (ኢዜአ) ፡- በአዲስ አበባ የመንግስት እና የህዝብ የንብረት አስተዳደርና አጠቃቀም በዲጂታል ቴክኖሎጂ አሰራር መተግበር የሚያስችል ሶፍትዌር ተመርቆ ወደ ሙሉ ትግበራ መገባቱን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ እንደገለጹት ሶፍትዌሩ የመንግስትና የህዝብ ሃብትን በስርዓት ለማስተዳደር፣ ብክነትን እና ብልሹ አሰራርን ለማስቀረት እንዲሁም ህንፃዎችን በመመዝገብ በትክክል አውቆ ለመጠቀም የሚያስችል ነው።


 

ሶፍትዌሩ በ20 የመንግስት ተቋማት ላይ ተሞክሮ ውጤታማነቱ የተረጋገጠ ሲሆን በተቀሩት የከተማ አስተዳደሩ ተቋማት ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናል ብለዋል።

የመንግስት ንብረት አስተዳደር ባለስልጣንና የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ሴፍትዌሩን በትብብር ማልማታቸውን ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስታውቀዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም