የፕሪሚየር ሊጉ ሰባተኛ ሳምንት ጨዋታዎች ከዛሬ ጀምሮ ይካሄዳሉ - ኢዜአ አማርኛ
የፕሪሚየር ሊጉ ሰባተኛ ሳምንት ጨዋታዎች ከዛሬ ጀምሮ ይካሄዳሉ

አዲስ አበባ ፤ ህዳር 27/2016 (ኢዜአ) ፡-የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሰባተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ዛሬ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በሚደረጉ ሁለት ጨዋታዎች ይጀመራል።
ወልቂጤ ከተማ ከሀምበሪቾ ዱራሜ ከቀኑ 9 ሰዓት ላይ ይጫወታሉ።
በ 5 ነጥብ በሊጉ 13ኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ወልቂጤ ከተማ በሊጉ ባደረጋቸው ያለፉት አምስት ተከታታይ ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻለው አንድ ጊዜ ብቻ ነው።
በሁለቱ ሲሸነፍ በሁለቱ አቻ ተለያይቷል።
በ2 ነጥብ 15ኛ ደረጃን በመያዝ ወራጅ ቀጠና ውስጥ የሚገኘው ሀምበሪቾ ዱራሜ በሊጉ ባደረጋቸው ያለፉት አምስት ጨዋታዎች በሶስቱ ሲሸነፍ በሁለቱ አቻ ወጥቷል።
ሀምበሪቾ ዱራሜ በሊጉ እስከ አሁን ምንም ጨዋታ አላሻነፈም።
ከምሽቱ 12 ሰዓት ፋሲል ከነማ ከወላይታ ድቻ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
በ12 ነጥብ 4ኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ፋሲል ከነማ በሊጉ ባደረጋቸው ያለፉት አምስት ጨዋታዎች በሶስቱ ሲያሸንፍ በሁለቱ ነጥብ ተጋርቷል።
ተጋጣሚው ወላይታ ድቻ በበኩሉ ባለፉት አምስት የሊጉ ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻለው አንድ ጊዜ ብቻ ነው።
በሁለቱ ሲሸነፍ በሁለቱ አቻ ወጥቷል።
ወላይታ ድቻ በ8 ነጥብ 8ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
የፕሪሚየር ሊጉ የሰባተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ነገም ቀጥሎ ሲውል መቻል ከአዳማ ከተማ ከቀኑ 9 ሰዓት፤ ባህር ዳር ከተማ ከሃዋሳ ከተማ ምሽቱ 12 ሰዓት ላይ ይጫወታሉ።
የሊጉ የሰባተኛ ሳምንት ጨዋታዎች እስከ ሕዳር 30 ቀን 2016 ዓ.ም ይቆያሉ።