አንጋፋው የኢትዮጵያ ሬዲዮ ጋዜጠኛ አስፋው ገረመው ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ - ኢዜአ አማርኛ
አንጋፋው የኢትዮጵያ ሬዲዮ ጋዜጠኛ አስፋው ገረመው ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ
አዲስ አበባ ፤ ህዳር 26/2016 (ኢዜአ) ፦ በኢትዮጵያ ሬዲዮ ከ30 ዓመታት በላይ በተለያዩ የኃላፊነት ደረጃዎች ሲያገለግል የቆየው ጋዜጠኛ አስፋው ገረመው ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።
ጋዜጠኛ አስፋው ገረመው "ይህ የኢትዮጵያ ሬዲዮ ነው" የሚለው የጣቢያውን መክፈቻ ድምፅ ጨምሮ አሁንም ድረስ አየር ላይ የሚገኙ ተወዳጅ ስራዎች ያሉት ጋዜጠኛ ነበር።
ኢትዮጵያን እንቃኛት፣ ከአድማስ ባሻገር፣ የሬዲዮ መዝናኛ፣ ዜና፣ የኪነ-ጥበባት ምሽት፣ የቅዳሜ መዝናኛ እና የመሳሰሉ ዝግጅቶች ላይም ደማቅ አሻራውን ማሳረፉን የኢቢሲ ዘገባ ያመለክታል።
ጋዜጠኛ አስፋው ገረመው የሁለት ልጆች አባትም ነበር።
የአንጋፋው የኢትዮጵያ ሬዲዮ ጋዜጠኛ አስፋው ገረመው የቀብር ሥነ-ሥርዓት በዛሬው ዕለት ቤተሰቦቹ፣ ወዳጅ ዘመዶቹና የቀድሞ የስራ ባልደረቦቹ በተገኙበት በአዲስ አበባ ቀጨኔ መድኃኒዓለም ቤተ-ክርስቲያን ተፈፅሟል።