በኦሮሚያ ክልል 18ኛው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በማያ ከተማ እየተከበረ ነው

ሐረር፤ ኅዳር 26/2016 (ኢዜአ)፡- በኦሮሚያ ክልል ደረጃ 18ኛው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀን በምስራቅ ሐረርጌ ማያ ከተማ እየተከበረ ነው።

"ብዝሃነትና እኩልነት ለአገራዊ አንድነት!" በሚል መሪ ሃሳብ እየተከበረ በሚገኘው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን ላይ ቀኑን የተመለከቱ የተለያዩ ኪነ ጥበባዊና ሌሎች ዝግጅቶች  እየቀረቡ ይገኛሉ።

በክብር እንግድነት የተገኙት የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ወይዘሮ ሰዓዳ አብዱረህማን ቀኑን አስመልክተው መልዕክት እንደሚያስተላልፉ ይጠበቃል።


 

በሥነ-ሥርዓቱ ላይ በጨፌ ኦሮሚያ የመንግስት ተወካይና የብልጽግና ፓርቲ የኦሮሚያ ክልል ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ፈቃዱ ተሰማን ጨምሮ  የፌዴራል፣  የአጎራባች እና የክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣናት፣ ምሁራን፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ታድመዋል።

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም