በለሚ እንጀራ ፋብሪካ ለሚሰሩ ሴቶች የገበያ ትስስርን ለማጠናከር እገዛ ይደረጋል - ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል

አዲስ አበባ፤ ህዳር 26/2016(ኢዜአ)፦ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና የስራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል በለሚ እንጀራ ፋብሪካ በመገኘት የስራ እድል የተፈጠረላቸውን ሴቶች የስራ እንቅስቃሴ ጎብኝተዋል።

በጉብኝቱ ላይም የእንጀራ ፋብሪካው ለሴቶች የስራ እድል ከመፍጠር በተጨማሪ የሚያመርተው እንጀራ ደረጃውን የጠበቀ፣ የተሻለ ጥራት ያለውና ጤፍን በግብአትነት የሚጠቀም ከመሆኑም ባለፈ አመራረቱ ንጽህናውን የጠበቀ መሆኑን ማየታቸውን ሚኒስትሯ ተናግረዋል።


 

በፋብሪካው የስራ እድል የተፈጠረላቸው ሴቶች ቤተሰብ አስተዳዳሪ በመሆናቸው ከመጠቀማቸውም ባለፈ ገበያ በማረጋጋት ረገድም አይነተኛ ሚና እንዲጫወት ገልጸው መስሪያ ቤታቸው የገበያ ትስስር ማጠናከር ላይ እንደሚያግዝም ቃል ገብተዋል።

ከንቲባ አዳነችም ሚኒስትሯ በስፍራው ተገኝተው ሴቶቹን ስላበረታቱና ለማገዝም ስለፈቀዱ ምስጋና ማቅረባቸውን ከከንቲባ ጽሕፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም