"የብዝኃነት" ቀን የኢትዮጵያውያንን ኅብረ ብሔራዊ አንድነት በሚያንጸባርቁ ዝግጅቶች በጅግጅጋ እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ ፤ ህዳር 26/2016 (ኢዜአ)፡-  የኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች በዓልን ምክንያት በማድረግ "የብዝኃነት" ቀን የኢትዮጵያውያንን ኅብረ ብሔራዊ አንድነት በሚያንጸባርቁ ዝግጅቶች በጅግጅጋ ከተማ በድምቀት እየተከበረ ነው።

በዝግጅቱ ላይ ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች የመጡ የባህል ቡድኖች ባህላዊ ትርዒታቸውን በማቅረብ ላይ ናቸው።


 

18ኛው የኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች በዓል  "ብዝኅነትና እኩልነት ለሀገራዊ አንድነት" በሚል መሪ ሃሳብ ከትናንት ጀምሮ በጅግጅጋ ከተማ በድምቀት መከበሩን ቀጥሏል። 

በዛሬው ዕለትም "የብዝኃነት" ቀን እየተከበረ ሲሆን፤ በስነ ስርዓቱ ላይም የኢትዮጵያዊያንን ኅብረብሔራዊ አንድነት የሚያንጸባርቁ የባህል የልምድ ልውውጥ ዝግጅቶች እየቀረቡ ነው። 

ትናንት ህዳር 25 ቀን 2016 ዓ.ም "የወንድማማችነት" ቀን የተከበረ ሲሆን፤ ቀኑን ምክንያት በማድረግ ጎዳና ላይ ሩጫ ውድድርና የባህል ትዕይንት ተካሂዷል።

በዕለቱ የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ኢብራሂም ዑስማን ለብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን የተዘጋጀውን የንግድ ትርኢትና ባዛር ከፍተዋል።

በቀጣይ ኅዳር-27 የአብሮነት፣ ኅዳር-28 የመደመር፣ ኅዳር-29 የኢትዮጵያ ቀን በሚሉ ስያሜዎች በልዩ ልዩ መርሃ ግብሮች በድምቀት የሚከበር ይሆናል።

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም