ቀጣይ ምዕራፍ ለሁለንተናዊ ለውጥ በሚል መሪ ቃል የምስጋና እና የሰላም ኮንፍረንስ ተካሔደ - ኢዜአ አማርኛ
ቀጣይ ምዕራፍ ለሁለንተናዊ ለውጥ በሚል መሪ ቃል የምስጋና እና የሰላም ኮንፍረንስ ተካሔደ

አዲስ አበባ ፤ ህዳር 25/2016 (ኢዜአ) ፦ የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች “ቀጣይ ምዕራፍ ለሁለተናዊ ለውጥ” በሚል መሪ ሃሳብ ያዘጋጀው የምስጋናና የሰላም ኮንፍረንስ ዛሬ በሚሊኒየም አዳራሽ ተካሂዷል፡፡
ለዘመናት ምላሽ ለተነፈጋቸው የሙስሊም ወገኖቻችን ጥያቄዎች፤ በለውጡ መንግስት የተሰጣቸውን ምላሽ መነሻ በማድረግ ''ቀጣይ ምዕራፍ ለሁለንተናዊ ለውጥ'' በሚል መሪ ቃል የምስጋና እና የሰላም ኮንፍረንስ መካሔዱን ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል።
ለውጡን ተከትሎ ብዝሃነትን ታሳቢ በማድረግ በዕኩልነት ለተሰጠው አገልግሎትና ለመጣው ፍትሃዊነት በህዝበ ሙስሊሙ ለጠቅላይ ሚኒስትራችን ዶክተር ዐቢይ አሕመድ፣ ለከተማ አስተዳደሩ እና ለእኔም ለሰጡኝ እውቅና ከልብ ላመሰግን እወዳለሁ ሲሉም ገልጸዋል።
በቀጣይም ለህዝቦች እኩልነት፣ ሰላም እና አብሮነትን ለማረጋገጥ፤ ፍትሀዊ አገልግሎት በመስጠት በከተማችን ከሚገኙ ከተለያዩ የሃይማኖት ተቋማት ጋር በቅርበት መስራታችንን የምንቀጥል ይሆናል ብለዋል።