ኢትዮጵያ እና ኳታር ሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን በሚያጠናክሩባቸው ጉዳዮች ዙርያ መከሩ

አዲስ አበባ ፤ ህዳር 25/2016 (ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያ እና ኳታር መካከል ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነት የሚያጠናክር ውይይት መካሄዱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ በኢትዮጵያ አዲስ የተሾሙትን የኳታር አምባሳደር ሳድ ሙባረክ ሳድ ጃፋሊ አልናይሚን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።   


 

አምባሳደር ምስጋኑ በዚህ ወቅት በሁለቱ አገሮች መካከል በኢንቨስትመንት፣ ልማት እና በሌሎች የሁለትዮሽ ግንኙነት መስኮች ያለው ግንኙነት መጠናከር አለበት ብለዋል።  
  
ተሿሚው አምባሳደር በኢትዮጵያ በሚኖራቸው የስራ ቆይታ መንግስት ሁለንተናዊ ድጋፍ እንደሚያደርግላቸው ገልፀው፤ መልካም የስራ ዘመን ተመኝተውላቸዋል።   

አምባሳደር ሳድ በበኩላቸው የሁለቱን አገራት ግንኙነት ለማሳደግ ቁርጠኛ መሆናቸውን እንደገለጹ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም