የኢትዮጵያ ብሪክስን መቀላቀል ከሩሲያ ጋር ያላትን ትብብር ያጠናክራል - ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ብሪክስን መቀላቀል ከሩሲያ ጋር ያላትን ትብብር ያጠናክራል - ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን

አዲስ አበባ፤ ህዳር 25/2016(ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ ብሪክስን መቀላቀሏ ከሩሲያ ጋር ያላትን ትብብር የበለጠ የሚያጠናክረው መሆኑን የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ገለጹ።
በሩሲያ ፌዴሬሽን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ቻም ኡጋላ ኡሪያት የሹመት ደብዳቤያቸውን ለሩሲያው ፕሬዝዳንት አቀርበዋል ፡፡
አምባሳደሩ የሹመት ደብዳቤያቸውን ባቀረቡበት ወቅት ፕሬዝዳንት ፑቲን ባስተላለፉት መልዕክት ኢትዮጵያና ሩሲያ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ከመሰረቱ 125 ዓመታትን ያስቆጠሩ ወዳጅ አገራት መሆናቸውን አንስተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በቅርቡ በሩሲያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት በማድረግ የተለያዩ የትብብር ስምምነቶች መፈረማቸው ግንኙነቱን ከፍ ወዳለ ደረጃ እንዳሻገረው መግለጻቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
ኢትዮጵያ ብሪክስን መቀላቀሏ ደግሞ የሁለቱን ሃገራት ግንኙነት የበለጠ እንደሚያጠናክረው ተናግረዋል፡፡