18ኛውን የብሔሮች ፣ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓልን በማስመልከት በጅግጅጋ ከተማ የ5 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር ተካሄደ - ኢዜአ አማርኛ
18ኛውን የብሔሮች ፣ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓልን በማስመልከት በጅግጅጋ ከተማ የ5 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር ተካሄደ

ጅግጅጋ ፤ ህዳር 25/2016 (ኢዜአ) ፡- 18ኛውን የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓልን በማስመልከት በጅግጅጋ ከተማ የ5 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር ተካሄደ።
ውድድሩ ከማለዳው 12 ከ30 ጀምሮ በከተማው ሰይድ መሀመድ አብደላ ሀሰን አደባባይ የተካሄደ ሲሆን የጅግጅጋ ከተማ ወጣቶች ተሳትፈዋል።
18ኛው የብሔሮች ፣ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል ከዛሬ ህዳር 25 እስከ ህዳር 29/2016 ዓ.ም ድረስ በፌዴሬሽን ምክር ቤት አስተባባሪነትና በሶማሌ ክልል አስተናጋጅነት "ብዝኅነትና እኩልነት ለሀገራዊ አንድነት" በሚል መሪ ሃሳብ በጅግጅጋ ከተማ በልዩ ልዩ ዝግጅቶች ይከበራል።
በዚህም ህዳር-25 የወንድማማችነት፣ ህዳር-26 የብዝሃነት፣ ህዳር-27 የአብሮነት፣ ህዳር-28 የመደመር፣ ህዳር-29 የኢትዮጵያ ቀን በሚሉ መሪ ስያሜዎች በተለያዩ ዝግጅቶች መከበሩን ጀምሯል።