በታንዛንያ በተከሰተ የመሬት መንሸራተት የ47 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለጸ

321

አዲስ አበባ ፤ ህዳር 24/2016 (ኢዜአ) ፦ በታንዛንያ ከባድ ዝናብ መጣሉን ተከትሎ በተከሰተ የመሬት መንሸራተት በትንሹ የ47 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገልጿል።

የአየር ንብረት ለውጥን ተከትሎ ከፓስፊክ ውቅያኖስ የሚነሳው ዝናብ አዘሉ የአሌ ኒኖ ክስተት ታንዛንያን ጨምሮ በኬኒያና በሶማልያ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ይገኛል።

በሰሜን ታንዛንያም ከቅዳሜ ጀምሮ እየጣለ የሚገኘው ነፋስ የቀላቀለ ዝናብ ባስከተለው የመሬት መንሸራተት አደጋ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን ዘጋርዲያን በዘገባው አስነብቧል።


 

በሰሜናዊ ታንዛንያ ካቴሽ ከተማ በተከሰተው አደጋ እስከ ትላንት ምሽት ድረስ በተንሹ የ47 ሰዎች ህይወት ማለፉንና 85 ሰዎች መጎዳታቸውን ተጠቅሷል።

በግዛቲቱ እየጣለ የሚገኘውን ነፋስ የቀላቀለ ዝናብ ተከትሎ የተጎጂዎች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል ያመለከተው ዘገባው ለአካባቢው ነዋሪዎች የማስጠንቀቂያ መልዕክት ከግዛቲቱ የአደጋ መከላከል ኮሚሽን መተላለፉንም ገልጿል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም