የአየር ንብረት ለውጥ ቀውስ ከ 12 ሆስፒታሎች አንዱን የመዝጋት አደጋን ደቅኗል - ኢዜአ አማርኛ
የአየር ንብረት ለውጥ ቀውስ ከ 12 ሆስፒታሎች አንዱን የመዝጋት አደጋን ደቅኗል

አዲስ አበባ፤ ህዳር 24/2016 (ኢዜአ)፦የካርበን ልቀትን መቆጣጠር ካልተቻለ በአለማችን ካሉ 12 ሆስፒታሎች አንዱ በአየር ንብረት ቀውስ ሙሉ በሙሉ አለያም በከፊል የመዘጋት አደጋ መደቀኑን ጥናት አመለከተ።
ይህ ጥናት የቀረበው በዱባዩ ኮፕ28 የመሪዎች የጤና ጉባኤ ላይ ነው።
የካርበን ልቀትን መቆጣጠር ካልተቻለ በሚያስከትለው የአየር ንብረት ቀውስ በአለማችን ካሉ 12 ሆስፒታሎች አንዱ ሙሉ በሙሉ አለያም በከፊል የመዘጋት አደጋ አንደተደቀነበት የሲተቪ ኒውስ ዘገባ ያመለክታል።
በክሮስ ዲፔንዳንሲ ኢኒሼቲቭ የሳይንስና ቴክኖሎሊ ዳይሬክተር ዶክተር ካረለ ማሎን በኮፕ 28 ዱባይ የጤና ጉባኤ ላይ ባቀረቡት ሪፖርት እንዳመለከቱት ለጥናት ከተወሰዱ ከ200ሺ 216 ሆስፒታል ናሙናዎች ከ12 አንዱ አደጋላይ ነው ።
የአየር ንብረት ለውጡ ሆስፒታሎች ላይ የሚያስከትለው አውሎ ንፋስ፣ የጎርፍ መጥለቅለቅ ወይም የደን ቃጠሎ ስራቸውን ያስተጓጉላል አለያም ወደ ሌላ ቦታ እንዲቀይሩ ያስገድዳቸዋል እንደ ሪፖርቱ ገለጻ።
ችግሩን መቅረፍ ካልተቻለም በምእተአመቱ መገባደጃ የአለማችን 16ሺ245 ሆስፒታሎች በአየር ንብረት ለውጡ ሙሉ በሙሉ አለያም በከፊል ይዘጋሉ ።
የአየር ንብረት ለውጥ በጤና ላይ የሚያደርሰውን ጉዳት ለመቀነስም የቅሪተ አካላት ነዳጅ አጠቃቀምን መቆጣጠር አስገዳጅ ነው።