በሕብረ ብሔራዊ ወንድማማችነትና እህትማማችነት ባጌጠችው  አዲስ አበባ 18ኛውን የብሄር ብሄረሰቦች ቀን አክብረናል - ከንቲባ አዳነች አቤቤ 

238

አዲስ አበባ ፤ ህዳር 23/2016 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያውያን በሕብረ ብሔራዊ ወንድማማችነትና እህትማማችነት ባስጌጧት የሁላችን ቤት በሆነችው አዲስ አበባ 18ኛውን የብሄር ብሄረሰቦች ቀን አክብረናል ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ 18ኛው የብሔር ብሔረሰቦች ቀን ማጠቃለያ የባህል ፌስቲቫል በከተማችን ተከናውኗል ሲሉም በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ገልጸዋል።


 

አክለውም ኢትዮጵያውያን በሕብረ ብሔራዊ ወንድማማችነትና እህትማማችነት ባስጌጧት የሁላችን ቤት በሆነችው አዲስ አበባ “ብዝሃነትና እኩልነት ለሃገራዊ አንድነት” በሚል መሪ ቃል 18ኛውን የብሄር ብሄረሰቦች ቀን ዛሬ ረፋድ ላይ አክብረናል ብለዋል።


 

ብዝሀነት ነባራዊ ሀቅ፣ መዋቢያችን፣ መድመቂያችን መሆኑን ተገንዝበን ከሃገራዊ አንድነታችን ጋር አስተሳስረን በትጉሀን እጆች ወደ ብልፅግና እየገሰገሰች ያለችውን ኢትዮጵያን በሁላችን ትጋት ራዕይዋን እውን ማድረግ እንቀጥላለን ሲሉም ከንቲባ አዳነች ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም