የብሄር፣ ብሄረሰቦችና ሕዝቦች ቀንን ምክንያት በማድረግ በአዲስ አበባ የባህል ፌስቲቫል እየተካሄደ ነው

150

አዲስ አበባ ፤ ህዳር 23/2016 (ኢዜአ) ፡-18ኛው የብሄር፣ ብሄረሰቦችና ሕዝቦች ቀንን ምክንያት በማድረግ በአዲስ አበባ የባህል ፌስቲቫል እየተካሄደ ነው።    

ፌስቲቫሉ በአዲስ አበባ ከተማ ወዳጅነት አደባባይ "ብዝሃነትና እኩልነት ለአገራዊ አንድነት" በሚል መሪ ሀሳብ በመካሄድ ላይ ይገኛል። 

በፌስቲቫሉ ላይ ከሁሉም ብሄር ብሄረሰቦች የተወከሉ ተሳታፊዎች  የባህል ምግቦች፣ አልባሳት እና ባህላዊ ውዝዋዜዎች እየቀረቡ ነው።  

በፌስቲቫሉ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ የክልልና ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ-ጉባኤዎች፣ የመዲናዋ ነዋሪዎችና ሌሎችም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።      

18ኛው የብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን በሀገር አቀፍ ደረጃ ህዳር 29 ቀን 2016 ዓ.ም በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ የሚከበር ይሆናል።  

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም