ኢትዮጵያ በደርባን እየተካሄደ ባለው የብሪክስ ሀገራት ስብሰባ እየተሳተፈች ነው

114

አዲስ አበባ፤ህዳር 23/2016(ኢዜአ ):- ኢትዮጵያ በደቡብ አፍሪካ ደርባን እየተካሄደ በሚገኘው የብሪክስ ሀገራት ስብሰባ ላይ እየተሳተፈች ነው።

በስብሰባው ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዢ ማሞ ምህረቱ ብሪክስ ሀገራት አቅማቸውን አሟጠው በመጠቀም ለማደግ የሚያደርጉትን ጥረት የሚያግዝ ነው ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ በታሪኳ በዲፕሎማሲ እንደምትታወቅ ያስረዱት አቶ ማሞ ምህረቱ የብሪክስ አባል ለመሆንም የቀደመ ታሪኳ እንደረዳት ጠቁመዋል፡፡

ብሪክስ በዓለም አቀፍ ደረጃ ብልጽግና እና ሰላም ለማምጣት የሚያደርገው ጥረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም