የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ካዛብላንካ የጭነት ማጓጓዝ በረራ ሊጀምር ነው - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ካዛብላንካ የጭነት ማጓጓዝ በረራ ሊጀምር ነው
አዲስ አበባ፤ ህዳር 22/2016(ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሞሮኮ - ካዛብላንካ አዲስ የጭነት ማጓጓዝ በረራ ሊጀምር መሆኑን አስታወቀ።
አየር መንገዱ ወደ ካዛብላንካ የሚያደርገው የጭነት በረራ በሰሜን አፍሪካ የመጀመሪያው መሆኑ ተገልጿል።
ይህም አየር መንገዱ በአፍሪካ የሚያደርጋቸውን የጭነት በረራዎች ቁጥር 34 እንደሚያደርሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል፡፡