ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ የጀመረቺው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር የአየር ንብረት ለውጥን በመቋቋም ዓለም ዓቀፍ የካርቦን ልቀትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ወሳኝ ነው

አዲስ አበባ፤ ህዳር 21/2016 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ እያካሄደቺው ያለው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር የአየር ንብረት ለውጥን በመቋቋም ዓለም ዓቀፍ የካርቦን ልቀትን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር ወሳኝነት እንዳለው ተገለጸ።

ኢትዮጵያ በተባበሩት አረብ ኢምሬቶች ዱባይ እየተካሄደ ባለው ኮፕ 28 የአየር ንብረት ጉባኤ ላይ የኢትዮጵያን የአረንጓዴ ዐሻራ መካነ ርዕይ(ፓቪሊዮን) አዘጋጅታለች።

ከአሜሪካ ቦስተን ኮሌጅ በኮፕ 28 የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ላይ እየተሳተፈ የሚገኘው ጃክ ሼይን የኢትዮጵያ የአረንጓዴ ዐሻራ መካነ ርዕይ የጎበኘ ሲሆን ኢትዮጵያ በአረንጓዴ አሻራ ኢኒሼቲቭ እያሳየቺው ያለው ለውጥ የሚደነቅ ነው ሲል ገልጿል።

በአረንጓዴ አሻራ ኢኒሼቲቭ አማካኝነትም ከ31 ቢሊዮን በላይ ችግኞችን መትከሏ ለዘርፉ ያላትን ቁርጠኝነት ያሳያል ብሏል።

በዚህም ኢትዮጵያ እያካሄደቺው ያለው የአረንጓዴ አሻራ እንቅስቃሴ የካርቦን ልቀትን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የበኩሏል አስተዋጽኦ እየተወጣች ትገኛለች ሲል ነው የገለጸው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም