ኢትዮጵያ በአረንጎዴ አሻራ እየሰራችው ያለው ስራ ለአፍሪካ ምሳሌ የሚሆን ነው - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ በአረንጎዴ አሻራ እየሰራችው ያለው ስራ ለአፍሪካ ምሳሌ የሚሆን ነው

አዲስ አበባ ፤ ህዳር 21/2016 (ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ በአረንጎዴ አሻራ እየሰራቺው ያለው ስራ ለአፍሪካ ምሳሌ መሆን እንደሚችል የናይጀሪያ የግብርናና የምግብ ዋስትና ሚኒስትር ገለጹ፡፡
ኢትዮጵያ በተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ዱባይ እየተካሄደ ባለው ኮፕ 28 የአየር ንብረት ጉባኤ ላይ አረንጓዴ አሻራ መካነ ርዕይ/ፓቪሊዮን ለይታ አቅርባለች።
የናይጄሪያ የግብርናና የምግብ ዋስትና ሚኒስትር አቡበከር ክያሪ ኮፕ 28 የአየር ንብረት ጉባኤ ላይ አረንጓዴ ዓሻራ መካነ ርዕይ/ፓቪሊዮን ጉብኝተዋል።
በጉብኝታቸውም ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ በአረንጓዴ አሻራ እያከናወነችው ያለው ተግባራት የሚያስደንቅ ነው ብለዋል፡፡
በኢትየጵያ እየተከናወነ ያለው የአረንጎዴ አሻራ ለናይጄሪያ ብሎም ለመላው አፍሪካ ምሳሌ መሆን ይችላልም ሲሉ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።
ናይጄሪያ የአረንጓዴ ልማት ላይ ተመሳሳይ ተግባራት እያከናወነች መሆኑን የጠቆሙት ሚነስትሩ ፤ ኢትየጵያ በአረንጓዴ አሻራ ያገኘችውን ይህን መሰል ውጤት ናይጄሪያ ልምድ መውሰድ ትፈልጋለች ብለዋል።
በመሆኑም ለዚህ የአረንጎዴ አሻራ ስኬት ሚስጥር ናይጄሪያ ወደ ኢትየጵያ በመምጣት ለመመልከት ከፍተኛ ተነሳሽነት እንደፈጠረባቸው ሚኒስትሩ አስታውቀዋል፡፡