ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከኩባው ፕሬዝዳንት ሚግዌል ዲያዝ-ካናል ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፤ ህዳር 21/2016 (ኢዜአ)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከኮፕ28 ጉባኤ ጎን ለጎን የኩባውን ፕሬዝዳንት ሚግዌል ዲያዝ-ካናልን አነጋገሩ።

ሁለቱ መሪዎች የአለም የአየር ጠባይ ለውጥ ኃላፊነትን፣ የሁለትዮሽ ትብብርን እና የብሔራዊ ልማት ጉዳዮችን የተመለከተ ውይይት ማድረጋቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት መረጃ ጠቁሟል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከኮፕ28 ጉባኤ ጎን ለጎን የኩባውን ፕሬዝዳንት ሚግዌል ዲያዝ-ካናልን ያነጋገሩት በኢትዮጵያ አረንጓዴ አሻራ መካነ ርዕይ/ፓቪሊዮን/ ነው፡፡

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም