ኢትዮጵያና እስራኤል የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር ተስማሙ - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያና እስራኤል የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር ተስማሙ

አዲስ አበባ፤ ህዳር 21/2016(ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ እና እስራኤል የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር መስማማታቸው ተገለጸ።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር አለልኝ አድማሱን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።
በውይይታቸው አምባሳደር ምስጋኑ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የቆየ የሁለትዮሽ ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር ተከታታይ የሀሳብ ልውውጥ ማድረግ እንደሚያስፈልግ መግለጻቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
ግንኙነቱን ለማጎልበትም በቀጣይ የሁለትዮሽ አሰራሮችን መፈተሽ እና የፖለቲካ ምክክር ማድረግ እንደሚገባም አምባሳደር ምስጋኑ ተናግረዋል።