በተዘጋጁ ስልጠናዎች የተገኙ ልምዶችን በተግባር ማረጋገጥ ከአመራሩ የሚጠበቅ ተቀዳሚ ጉዳይ ነው - አቶ አደም ፋራህ - ኢዜአ አማርኛ
በተዘጋጁ ስልጠናዎች የተገኙ ልምዶችን በተግባር ማረጋገጥ ከአመራሩ የሚጠበቅ ተቀዳሚ ጉዳይ ነው - አቶ አደም ፋራህ

አዲስ አበባ ፤ ህዳር 21/2016 (ኢዜአ) ፦ በተዘጋጁ ስልጠናዎች የተገኙ ልምዶችን በተግባር ማረጋገጥ ከአመራሩ የሚጠበቅ ተቀዳሚ ጉዳይ ነው ሲሉ የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት እና የዋና ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ አደም ፋራህ ተናገሩ።
አቶ አደም ፋራህ በኢሉ አባቦር ዞን እየተሰጠ ባለው 4ኛ ዙር የመንግስት አመራር አካላት ስልጠና ላይ እየተሳተፉ ከሚገኙ ሰልጣኞች ጋር ተወያይተዋል።
በተያያዘም በዞኑ በተለያዩ አካባቢዎች እየለሙ የሚገኙ ልዩ ልዩ የልማት ስራዎችንም ተዘዋውረው መጎብኘታቸውን ከብልጽግና ፓርቲ ማህበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
በቀጣይ መሰል የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸው ከዚህ በፊት በተዘጋጁ ስልጠናዎች የተገኙ ልምዶችን በተግባር ማረጋገጥ ከአመራሩ የሚጠበቅ ተቀዳሚ ጉዳይ ነው ሲሉም አቶ አደም ተናግረዋል።