520 ሺህ ኩንታል ዩሪያ ማዳበሪያ የጫነች መርከብ ጅቡቲ ወደብ ደርሳለች-የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ

አዲስ አበባ ፤ ህዳር 20/2016 (ኢዜአ) ፦ 520 ሺህ ኩንታል ዩሪያ የአፈር ማዳበሪያ የጫነች መርከብ ጅቡቲ ወደብ መድረሷን የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አስታወቀ።

ተጨማሪ 615 ሺህ ኩንታል ኤን ፒ ኤስ ቦሮን የጫነች መርከብ ነገ ህዳር 21 ቀን 2016 ዓ.ም ጅቡቲ ወደብ እንደምትደርስ ይጠበቃል ብሏል።

በዚህም እስከአሁን 2 ሚሊዮን 84 ሺህ 685.1 ኩንታል ዩሪያ መጓጓዙን ከኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ እስክ ታህሳስ 3 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ ተጨማሪ 1 ሚሊዮን 130 ሺህ ኩንታል ኤን ፒ ኤስ ቦሮን ወደብ ይደርሳል ተብሎ እንደሚጠበቅም አስታውቋል።

የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን (ኢግሥኮ) ለ2016/17 የምርት ዘመን ከውጭ ከገዛው የአፈር ማዳበሪያ ውስጥ እስከ ዛሬ ህዳር 20 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ በአምስት ዙሮች 2 ሚሊዮን 84 ሺህ 685.1 ኩንታል ዩሪያ መጓጓዙንም ጨምሮ ገልጿል።

ከዚህ ውስጥም 1 ሚሊዮን 92 ሺህ 178 ኩንታል ዩሪያ ከጂቡቲ ወደብ ወደ ሀገር ውስጥ ተጓጉዞ ለአርሶ አደር ዩኒየኖች እየተሰራጨ መሆኑን ጠቁሟል።

የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ የአፈር ማዳበሪያን በባሕር እና በየብስ የማጓጓዙን ሂደት በስኬት እያከናወነ መሆኑን ገልጾ የድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን የማጓጓዙ ሂደት ውጤታማ በሆነ መልኩ እንዲከናወን ያለሰለሰ ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛሉም ብሏል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም