በስፖርት ማህበራዊ ትስስርን በማጠናከር ለዘላቂ ሰላም መጠቀም ይገባል

አሶሳ፤ ህዳር 20/2016 (ኢዜአ)፡- በስፖርት ማህበራዊ ትስስርን በማጠናከር ለዘላቂ ሰላም መስፈን መጠቀም ይገባል ሲሉ  የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል  ዋና አፈጉባኤ ዶክተር ተመስገን ዲሳሳ አስገነዘቡ።

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል 18ኛውን የብሄር ብሄረሰቦች ቀን  በዓል ምክንያት በማድረግ በመተከል ዞን  ግልገል በለስ ከተማ ዛሬ የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር ተካሂዷል።


 

የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ ዶክተር ተመስገን ዲሳሳ በዚሁ ጊዜ እንዳሉት ስፖርት የሚያስገኘውን ሁለንተናዊ ጠቀሜታ ለዘላቂ ሠላም ማዋል ይገባል።

"ስፖርት የህብረተሰቡን ማህበራዊ ትስስር ለማጠናከር የላቀ ጠቀሜታ አለው " ያሉት ዋና አፈ ጉባኤው በዚህም ዘርፉን ለዘላቂ ሰላም መስፈን መጠቀም እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

የውድድሩ ዓላማም በዓሉን ምክንያት በማድረግ የእርስ በርስ ግንኙነትን ማጠናከር መሆኑን የገለጹት ደግሞ የክልሉ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር የሱፍ አልበሽር ናቸው።

በዚሁ በሶስት ኪሎ ሜትር  የጎዳና ላይ የሩጫ ውድድር የክልሉ ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ የግልገል በለስ ከተማና አካባቢው ነዋሪዎች ተሳትፈዋል።

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም