ተቋርጦ የቆየው የኢትየጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ ይጀመራል - ኢዜአ አማርኛ
ተቋርጦ የቆየው የኢትየጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ ይጀመራል

አዲስ አበባ ፤ ህዳር 20 /2016 (ኢዜአ) በአለም አቀፍ ውድድሮች ምክንያት ባለፉት 27 ቀናት ተቋርጦ የቆየው የኢትየጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ በሚደረጉ ሁለት ጨዋታዎች ይጀመራል፡፡
ዛሬ ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ድሬዳዋ ከነማ ከወላይታ ዲቻ ፤ ከምሽቱ አስራ ሁለት ሰዓት አምበሪቾ ዱራሚ ከፋሲል ከነማ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡
ሊጉ ነገም ቀጥሎ የሚውል ሲሆን ዘጠኝ ሰዓት ኢትዮጵያ መድህን ከመቻል ፤ በአስራ ሁለት ሰዓት ሻሸመኔ ከተማ ከወልቂጤ ከተማ የሚጫወቱ ይሆናል።
ጨዋታዎቹ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ይካሄዳሉ፡፡
ሊጉን ቅዱስ ጊዮርጊስ በ13 ነጥብ ሲመራ ሻሸመኔ ከነማ በአንድ ነጥብ የሊጉ መጨረሻ ላይ ተቀምጧል፡።