ቀጥታ፡

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአማካሪ ኮሚቴ የተለያዩ አጀንዳዎችን አፀደቀ

አዲስ አበባ ፤ ሕዳር 19/2016 (ኢዜአ)፡- በኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአማካሪ ኮሚቴ ነገ በሚካሄደው የምክር ቤቱ 7ኛ መደበኛ ጉባዔ የሚቀርቡ አጀንዳዎችን አጽድቋል፡፡

በነገው እለት በሚያካሂደው የምክር ቤቱ 7ኛ መደበኛ ጉባዔ ላይ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዳኛ ስንብትን በተመለከተ ለምክር ቤቱ በአጀንዳነት እንዲቀርብ አማካሪ ኮሚቴው በመሉ ድምፅ ወስኗል፡፡

በተጨማሪም ነገ በሚደረገው የምክር ቤቱ 6ኛ ዙር 3ኛ ዓመት 7ኛ መደበኛ ጉባዔ ላይ የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅርቦት እና የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ማሻሻያ አዋጅ በአጀንዳነት እንዲቀርብ በሙሉ ድምፅ ማፅደቁን ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማህበራዊ ትስስር ገፅ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

 

 

 

 

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም