ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አዲስ የማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ አዘጋጀ

አዲስ አበባ ፤ህዳር 19/2016 (ኢዜአ):-የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አዲስ የማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ ማዘጋጀቱን የባንኩ ገዥ ማሞ ምህረቱ ገለጹ። 

የብሔራዊ ባንኩ ገዥ ማሞ ምህረቱ፤ ረቂቅ አዋጁ የባንኩን ነፃነትና ተጠያቂነት ለማረጋገጥና የተሻለ የአሰራር ሥርዓት ለመፍጠር በሚያስችል መልኩ መዘጋጀቱን ገልፀዋል። 

ከተመሰረተ ስምንት አስርት ዓመታትን  ያስቆጠረውን ባንክ  ከዓለምና ከኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ ጋር ለማጣጣም ዘመናዊና ቀልጣፋ አሰራር መዘርጋት ወሳኝ ነው ብለዋል።

ለዚህ ደግሞ የባንኩን ማቋቋሚያ አዋጅ ማሻሻል ተገቢ መሆኑን በመጥቀስ።

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም