ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) እና ልዑካን ቡድናቸው የኢትዮ- ቼክ የትብብር መስኮች ጋር የተያያዙ ስፍራዎችን ጎበኙ - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) እና ልዑካን ቡድናቸው የኢትዮ- ቼክ የትብብር መስኮች ጋር የተያያዙ ስፍራዎችን ጎበኙ

አዲስ አበባ፤ህዳር 19/2016(ኢዜአ):-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) እና ልዑካን ቡድናቸው የኢትዮ- ቼክ የትብብር መስኮች ጋር የተያያዙ ስፍራዎችን ጎብኝተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩና ልዑካን ቡድናቸው በቼክ ሪፐብሊክ ቆይታቸው እንደ ግብርና፣ ቱሪዝም እና ባሕል ባሉ በመስፋፋት ላይ ካሉ የኢትዮ- ቼክ የትብብር መስኮች ጋር የተያያዙ ስፍራዎችን መጎብኘታቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።