አብርሆት ቤተመጻሕፍት የቴክኖሎጂ እና የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ሰልጣኞችን ተቀበለ - ኢዜአ አማርኛ
አብርሆት ቤተመጻሕፍት የቴክኖሎጂ እና የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ሰልጣኞችን ተቀበለ
አዲስ አበባ፤ ህዳር 18/2016 (ኢዜአ)፦ የአብርሆት ቤተመጻሕፍት አምስተኛ ዙር የቴክኖሎጂ እና የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ሰልጣኞችን ዛሬ ተቀብሏል።
ለሰልጣኞቹም የቤተመጻሕፍቱ ዳይሬክተር ኢንጂነር ውብአየሁ ማሞ አቀባበል ያደረጉ ሲሆን የእንኳን ደህና መጣቹ መልእክትም አስተላልፈዋል።
አብርሆት ቤተመጻሕፍት ቀደም ሲልም በአራት ዙሮች 500 ሰልጣኞችን የተቀበለ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን በአሁኑ ዙር የከፍተኛ የትምህርት ተቋማትና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን ጨምሮ መስፈርቱን ያሟሉ 200 ተማሪዎችን በመቀበል ለ4 ወራት የሚሰጠውን ስልጠና እንዲቀላቀሉ ተደርጓል።
እነዚህ ተማሪዎች በቆይታቸው Data Structure ፣ Algorithm እንዲሁም የ Arteficial Intelligence ስልጠና እንደሚወስዱ ተገልጿል።
ሰልጣኞቹ የተማሩትን የቴክኖሎጂ እውቀት በመጠቀምም ችግር ፈቺ አንዲሁም አለምአቀፋ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ የሚያስችላቸው መሆኑን አብርሆት ቤተመጻሕፍት ለኢዜአ የላከው መረጃ ያመለክታል።