ኢትዮጵያ እና ቼክ ሪፐብሊክ በመከላከያ ዘርፍ የቆየ ትብብራቸውን በማስፋት በግብርና፣ በማዕድን ልማት እና ቱሪዝም ትብብራቸውን ለማጠናከር ወሰኑ

አዲስ አበባ ፤ ህዳር 18/2016 (ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ እና ቼክ ሪፐብሊክ በመከላከያ ዘርፍ የቆየ ትብብራቸውን በማስፋት በግብርና፣ በማዕድን ልማት እና ቱሪዝም ትብብራቸውን ለማጠናከር ወስነዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቼክ ሪፐብሊክ መንግስት ጽሕፈት ቤት በጠቅላይ ሚኒስትር ፔትር ፊያላ በይፋዊ አቀባበል ሥነ ሥርዓት አቀባበል ተደርጎላቸዋል።


 

ሁለቱ መሪዎች ባካሄዱት የሁለትዮሽ ውይይትም በመከላከያ ዘርፍ የቆየ ትብብራቸውን በማስፋት በግብርና፣ በማዕድን ልማት እና ቱሪዝም ትብብራቸውን ለማጠናከር መወሰናቸው ተገልጿል።

የቼኩ ጠቅላይ ሚኒስትር ባለፉት ቅርብ ሳምንታት ኢትዮዽያን በመጎብኘት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ጋር ውይይት አድርገው እንደነበር የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም