ኢትዮ-ቴሌኮም አምስተኛው ትውልድ (5ጂ) የኢንተርኔት ኔትወርክ አገልግሎት በጅግጅጋ ከተማ አስጀመረ

አዲስ አበባ ፤ ህዳር 18/2016 (ኢዜአ) ፡- ኢትዮ-ቴሌኮም አምስተኛው ትውልድ (5ጂ) የኢንተርኔት ኔትወርክ አገልግሎት በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ አስጀምሯል።

አገልግሎቱን የኢትዮ-ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ በይፋ አስጀምረውታል።

በመርሃ ግብሩ የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ኢብራሒም ኡስማንን ጨምሮ ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል።

አገልግሎቱ በአገሪቱ በቴክኖሎጂ የታገዘ አገልግሎት አሰጣጥን ይበልጥ በማዘመን ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ በእጅጉ ያግዛል ተብሏል።

የ (5ጂ) የኔትወርክ አገልግሎት ወደ ሌሎች የአገሪቱ አካባቢዎችም ተደራሽ የማድረግ ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ አረጋግጠዋል።

ኢትዮ-ቴሌኮም ከዚህ ቀደም የ (5ጂ) የኢንተርኔት ኔትወርክ በአዲስ አበባና በአዳማ ከተማ ማስጀመሩ ይታወሳል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም