አንጎላ ከኢትዮጵያ ጋር በግብርናው ዘርፍ በትብብር መስራት እንደምትፈልግ ፕሬዝዳንት ጆአዎ ማኑዌል ጎንካልቬስ ሎሬንኮ ገለጹ

180

አዲስ አበባ ፤ ህዳር 18/2016 (ኢዜአ) ፡-አንጎላ ከኢትዮጵያ ጋር በግብርናው ዘርፍ በትብብር መስራት እንደምትፈልግ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ጆአዎ ማኑዌል ጎንካልቬስ ሎሬንኮ ገለጹ። 
አምባሳደር ፍርቱና ዲበኮ የሹመት ደብዳቤያቸውን ለአንጎላ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ጆአዎ ማኑዌል ጎንካልቬስ ሎሬንኮ አቅርበዋል ። 

በስነ ስርዓቱ ላይ ኢትዮጵያ በንግድ ፣በግብርና በቱሪዝም እና በኢንቨስትመንት ዘርፎች ከአንጎላ ሪፐብሊክ ጋር በቅርበት መስራት እንደምትፈልግ  አምባሳደር ፍርቱና ለፕሬዝዳንቱ ገልፀዋል ። 


 

ፕሬዝዳንቱ በበኩላቸው ኢትዮጵያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በግብርናው ዘርፍ ከፍተኛ ውጤት እያስመዘገበች እንደምትገኝ ገልፀው፤ በትብብር መስራት እንደሚፈልጉ መግለፃቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም