የኢትዮጵያን የቱሪዝም ሃብቶች ያስተዋወቀ ፎረም በቤጂንግ ተካሄደ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያን የቱሪዝም ሃብቶች ያስተዋወቀ ፎረም በቤጂንግ ተካሄደ

አዲስ አበባ ፤ ህዳር 18/2016 (ኢዜአ) ፡- የኢትዮጵያን የቱሪዝም ፀጋዎችና የኢንቨስትመንት እድሎችን ለቻይና ዜጎች ለማስተዋወቅ ያለመ የቱሪዝም ፕሮሞሽን ፎረም በቻይና ቤጂንግ ተካሂዷል፡፡
በፎረሙ ላይ በቻይና የሚገኙ አስጎብኚ ድርጅቶች እና በቱሪዝም ፕሮሞሽን ዘርፍ የተሰማሩ ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
የቱሪዝም ሚኒስትር አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ የኢትዮጵያን የቱሪዝም ሃብቶች፣ ምርቶች እና የኢንቨስትመንት እድሎችን አስመልክቶ ለታዳሚዎች ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
የኢትዮጵያ መንግስት ለቱሪዝም ዘርፍ ልማት የሰጠው ልዩ ትኩረትን በተመለከተም አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።
በዚህም ኢትዮጵያ ለቻይናውያን ጎብኚዎች ተመራጭ የሆኑ የቱሪዝም ምርቶችና አገልግሎቶች እየተስፋፉ መሆኑን ገልጸው የኢትዮጵያን ፈረጀ-ብዙ የቱሪዝም መስህቦች እንዲጎበኙ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ፎረሙን ያዘጋጀው በቻይና የኢትዮጵያ ኤምባሲ ሲሆን በሁለቱ ሀገራት መካከል የቱሪዝም ትስስሮችንና ትብብሮችን ማጠናከር እንደሚያስፈልግ መገለጹን ከቱሪዝም ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡