የሰላም ምክር ቤት ሁለተኛ ጉባኤውን እያካሄደ ነው

አዲስ አበባ ፤ ህዳር 18/2016 (ኢዜአ) ፡- አገር አቀፉ የሰላም ምክር ቤት ሁለተኛ ጉባኤውን እያካሄደ ነው  ።

በመድረኩ የሰላም ሚንስትሩ ብናልፍ አንዱዓለምን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ የኃይማኖት አባቶችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል። 


 

የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ሥዩም መስፍን በዚሁ ጊዜ፤ ሰላም ሁለት ገጽታ የያዘ ቁልፍ ጉዳይ ነው ብለዋል። 

በአንድ በኩል ሰላም ልማትን ለማፋጠን ዴሞክራሲና መልካም አስተዳደርን ለማረጋገጥ አስቻይ ሚና አለው ብለዋል።

በሌላ በኩል ሰላም በራሱ በግብነት የሚከወን እራሱን የቻለ ተግባር መሆኑን ጠቁመዋል።

የሰላም ግንባታ ፍሬያማ እንዲሆን ከሁሉም ለሁሉም በሚል መንፈስ ተቋማት ኃላፊነት ወስደው በባለቤትነት የሚከውኑት ቁልፍ የጋራ ተልዕኮ መሆኑን አመላክተዋል።

ምክር ቤቱ እስካሁን የተከናወኑ የሰላም ግንባታ ጥረቶች በትኩረት በመገምገም በቀጣይ ችግሮቹን ለመቅረፍ የሚያስችሉ አቅጣጫዎችን እንደሚያስቀምጥ ይጠበቃል።

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም