አፈ-ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር የ18ኛው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል ቅድመ ዝግጅትን ለመመልከት ጂግጂጋ ገቡ

አዲስ አበባ ፤ ህዳር 18/2016 (ኢዜአ) ፡- የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር እና ሌሎች ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች 18ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል ቅድመ ዝግጅትን ለመመልከት ሶማሌ ክልል ጂግጂጋ ከተማ ገብተዋል፡፡

በቆይታቸውም የሶማሌ ክልላዊ መንግሥት እንግዶችን ለመቀበልና በዓሉን በድምቀት ለማክበር እያደረገ ያለውን የቅድመ ዝግጅት ሥራ በመገምገም በቀሪ ሥራዎች ላይ አቅጣጫ ያስቀምጣል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከፌዴሬሽን ምክር ቤት የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

18ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል «ብዝኃነትና እኩልነት ለሀገራዊ አንድነት» በሚል መሪ ሀሳብ ይከበራል።

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም