ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) እና መራሄ መንግሥት ካርል ኔሃመር የሀገራቱን ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙርያ መክረዋል 

አዲስ አበባ ፤ ህዳር 18/2016 (ኢዜአ) ፡-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) እና የኦስትሪያው መራሄ መንግሥት ካርል ኔሃመር የሁለቱ አገሮችን ግንኙነትን የበለጠ ለማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙርያ መምከራቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት ሀላፊ ቢልለኔ ስዩም ተናገሩ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቪየና- ኦስትሪያ 20ኛውን የተባበሩት መንግሥታት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት ጠቅላላ ጉባዔ ተሳትፎ በተጓዳኝ ከኦስትሪያው መራሄ መንግሥት ካርል ኔሃመር ጋር መክረዋል።

ሁለቱ መሪዎች በውይይታቸው በኢትዮ- ኦስትሪያ ግንኙነት፣ በልማት ትብብር እና በሌሎች መስኮች ላይ ትስስራቸውን ስለሚያጠናክሩባቸው መንገዶች  መምከራቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት ሀላፊ ቢልለኔ ስዩም ተናግረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በተመድ የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት ጠቅላላ ጉባዔ ያካፈሉት ተሞክሮ ኢትዮጵያ በለውጥ ተምሳሌትነት እንድትታይ ያስቻለም እንደሆነ አስታውቀዋል።

ከጉባኤው ጎን ለጎንም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከኦስትሪያው መራሄ መንግሥት ካርል ኔሃመር ያደረጉት ውይይት የኢትዮጵያና ኦሰትሪያን ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር የሚያስችሉ ጉዳዮች የተነሱበት መሆኑን ገልጸዋል።

ከዚህ ቀደም በሀገራቱ መካከል ባልነበሩ ሌሎች የትብብር መስኮች ላይ በትኩረት ለመስራት የሚያስችል ምክክር እንዳካሄዱ  ነው የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት  ሀላፊዋ ያስታወቁት ።

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም