ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ በፆታዊ ጥቃት ላይ በሚመክረው መድረክ ለመካፈል ደቡብ አፍሪካ ገቡ

አዲስ አበባ ፤ ህዳር 18/2016 (ኢዜአ)፡- ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ በሴቶች እና ልጃገረዶች ላይ የሚደርሰውን ፆታዊ ጥቃት ለማስቆም በሚመክረው ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ ደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ ገብተዋል፡፡

ፕሬዚዳንቷ ፕሪቶሪያ ሲደርሱ በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሙክታር ከድር (ዶ/ር) አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ጉባኤው ትናንት የተጀመረ ሲሆን ዛሬም ቀጥሎ እንዲሚውል በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሙክታር ከድር (ዶ/ር) ማህበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም