ቀጥታ፡

18ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በባህሬን ተከበረ

አዲስ አበባ ፤ ህዳር 17/2016 (ኢዜአ) ፦ በባህሬን የኢትዮጵያ ቆንስላ ጀኔራል 18ኛውን የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀንን ‘’ብዝኃነትና እኩልነት ለሀገራዊ አንድነት’’ በሚል መሪ ሀሳብ አክብሯል።

በዝግጅቱ ላይ በባህሬን የሚኖሩ ከአራት መቶ በላይ ኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያን፣ የኢትዮጵያ ወዳጆችና ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል።

በባህሬን የኢትዮጵያ ቆንስል ጄኔራል አምባሳደር ሽፈራው ገነቲ በዝግጅቱ ላይ መልዕክት ማስተላለፋቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ይጠቁማል።

በመልዕክታቸውም ኢትዮጵያ የብዙ ቋንቋዎች፣ ባህልና እሴቶች ባለቤት በመሆኗ ሁሉም ዜጋ በመደመር ለሀገራችን ሁለንተናዊ ሰላምና ዕድገት በጋራ መቆም አለበት ብለዋል።

የዘንድሮው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀንን ስናከብር ባለፉት ዓመታት በሀገራችን የተገኙት ስኬቶችን ለማስቀጠል ቃል-ኪዳን በማደስ መሆን እንዳለበትም አምባሳደሩ ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም