ቀጥታ፡

የግብርና ሚኒስትሩ በሲዳማ ክልል የእንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ፕሮጀክት የልማት እንቅሰቃሴን  እየጎበኙ ነው

ሀዋሳ ፤ ህዳር 17/2016 (ኢዜአ)፡- የግብርና ሚኒስትር ዶክተር ግርማ አመንቴ ከዓለም ባንክ የሥራ ኃላፊዎች ጋር በመሆን በሲዳማ ክልል በእንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ፕሮጀክት ድጋፍ የተከናወኑ የልማት ስራዎችን እየጎበኙ ነው።


በጉብኝቱ ላይ የግብርና ሚኒስትር ዶክተር ግርማ አመንቴን ጨምሮ በዓለም ባንክ የኢትዮጵያ፣ የኤርትራ፣ የሱዳንና የደቡብ ሱዳን ካንትሪ ዳይሬክተር ኦስማን ዲዮን ተገኝተዋል።


 

እንዲሁም የሲዳማ ክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና የፕሮጀክቱ አስፈጻሚ ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል ።

አመራሮቹ በክልሉ በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙትን የእንስሳትና ዓሳ ዘርፍ የልማት ሥራዎችን እየጎበኙ ይገኛሉ።

አሁን ላይ በክልሉ በዳሌ ወረዳ ደቡብ መሰንቀላ ቀበሌ የሚገኘውን የወጣቶች ዶሮ እርባታ ማዕከል በመጎብኘት በልማቱ የተሳተፉ ወጣቶችን አበረታተዋል።

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም