አቶ በላይነህ ክንዴ ለለሚ እንጀራ ፋብሪካ ሶስት ተሽከርካሪዎችን አበረከቱ - ኢዜአ አማርኛ
አቶ በላይነህ ክንዴ ለለሚ እንጀራ ፋብሪካ ሶስት ተሽከርካሪዎችን አበረከቱ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 17/2016 (ኢዜአ)፦ አቶ በላይነህ ክንዴ ለለሚ እንጀራ ፋብሪካ ሰራተኞች ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ሶስት መለስተኛ ተሽከርካሪዎችን አበረከቱ።
አቶ በላይነህ ክንዴ ድጋፉን ለአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ አስረክበዋል፡፡
ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላልፉት መልዕክት “የለሚ እንጀራ ፋብሪካ በሙሉ አቅሙ ማምረት እንዲችል እያደረግን ባለው ጥረት በፋብሪካው ለሚሰሩ እናቶች ማመላለሻ የሚውል ሶስት መለስተኛ ተሽከርካሪዎች በስጦታ ያበረከቱትን አቶ በላይነህ ክንዴን ላመሰግን እወዳለሁ” ብለዋል።